ጥር 27, 2026

ኬላ ከተማ፣16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የኬላ-ቱሉቦሎ አስፓልት መንገድ ፕሮጀከት ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በአስፓልት መንገዱ ምርቃት በክብር እንግድነት የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር እንደሻው ጣሰው(ደ/ር)፣የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚ/ዴኤታ ክቡር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵ ክልል በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት አባላትና ካቢኔዎች፣ የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንገስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት የምርቃት ሥነ-ስርዓት ተከናውኗል፡፡

የአስፓልት መንገዱ ተጠናቆ ስራ መጀመሩ ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው ያሉት የክልሉ ፕሬዝዳንት በተለይ የዜጎችን የበርካታ ዓመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄን በመፍታት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን፣ ባህላዊ ቁርኝትን፣ ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በሰዓታት ልዩነት በመሸጥ ለራሱ ሚያስፈልገውን ሸቀጥ ደግሞ በመሸመት ህይወቱን ማደላደል እንደሚያስችለው ክቡር ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም የብልጽግናን ልዕልና ማረጋገጥ የሚያቸለው ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የሰላም፣ የልማት፣ የአብሮነት እና አንገብጋቢ የሚባሉ የወጣቱንና የአቅመ ደካሞችን ጥያቄዎች መንግሰት ትኩረት ሰጥቶ ደረጃ በደረጃ መመለስ ሲችል ህዝብና መንግስት ተሳስረው ለአንድ ዓላማ በመቆም የሀገራችንን ብልጽግና በአስተማማኝ ማረጋገጥ እንደምንችል እሙን ነው ብለዋል፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚ/ዴኤታ ክቡር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር) መንግሰት በ10 ዓመቱ ዕቅድ ለመሠረተ-ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ የዚህ አስፓልት መንገድ ተጠናቆ ስራ መጀመር አንዱ ማሳያ ነው ያሉት መንገድ ስልጣኔን፣ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር የብልጽግናን ጉዞ ከማረጋገጡም ባሻገር የሀገሪቱን የዕድገት ከፍታን በማብሰር ሀገራችንን ብሔራዊ ኩራት ለማሳደግ መሠረተ-ልማቶችን በፍጥነትና በጥራት ሠርቶ ለህብረተሰቡ ማስረከብ ተገቢነቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

አስፓልት መንገዱ ግንባታ የተራራቁ ወገኖችን በማቀራረብ ዘረፈ-ብዙ ማሀበራዊና ባህላዊ ትስርን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲያስችል በየደረጃው የሚገኝ የመንግሰት መዋቅርና መላው ህብረተሰብ ለመንገዱ ጥበቃና እንክብካቤ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ብለዋል ሚኒስቴር ዴኤታው፡፡

የኬላ-ቱሉቦሎ አስፓልት መንገድ ፕሮጀከት 83 ኪ.ሜ ሲሆን ይህን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ 1.3 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር እንደፈጀ በምርቃት ሥነ-ሰርዓቱ ላይ በዝርዝር ተገልጿል፡፡

Posted in: ዜና