ጥቅምት 30, 2026
አዲስ አበባ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና UN-Habitat በጋራ ያዘጋጁት የዓለም የከተሞች ቀን “ከተማን በማደስ በኢትዮጵያ ከተሞች ለሁሉም ምቹና ተስማሚ የመኖሪያ ቤት ማረጋጋጥ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መካሄድ ጀምሮአል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢንጂነር ሙሐመድ አብድራህማን የከተሜነት ዕድገት ለኢትዮጵያ ከታላላቅ የልማት ዕድሎች አንዱ በመሆኑ ከተሞቻችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የፈጠራ ሥራዎች፣ የቴክኖሎጂ እድገትና የማኅበራዊ ለውጥ ማዕከላት ለማድረግ እየሠራን ነው ብለዋል ።
ነገር ግን በዓመት 5.4 በመቶ የሚደርሰው ፈጣን የከተሜነት ዕድገት በመኖሪያ ቤት፣ በመሠረተ ልማት፣ በመሠረታዊ አገልግሎቶች፣ በመሬት አስተዳደር፣ በማዘጋጃ ቤቶች የራስ ገቢ ማሰባሰብና በከተማ ፋይናንስ አቅም ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ የገለጹት ክቡር ሚኒስትሩ ። እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የተቀናጀ እርምጃ፣ የረጅም ጊዜ ዕቅድና የዜጎቻችንን ፍላጎትና አቅም ያገናዘቡ ስትራቴጂያዊ እቅዶች እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ያስጀመረችው ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ 2025–2050 የከተማ እድገትን ለማፋጠን፣ የተቋማትና የማዘጋጃ ቤቶችን አቅም ለማጠናከር፣ የሀገር ውስጥ ሀብትን ለማሰባሰብና ለረጅም ጊዜ የቆዩ የከተማ ልማት ተግዳሮቶችን በሥርዓት በተደራጀ፣ በተቀናጀና ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል ክቡር ሚኒሰትር ።
ስትራቴጂው የኮሪደር ልማትን በማስፋፋት፣ የመኖሪያ ቤት ዕድሎችን በማሳደግ፣ ተቋቋሚና አካታች የከተማ ልማትን በማበረታታት፣ እንዲሁም የከተሞችን የኢኮኖሚ መሠረት በማጠናከር የኢትዮጵያን የከተማ ለውጥ ሂደት ይበልጥ ያፋጥናል ስሉም ገልጸዋል ።
ኢትዮጵያ በ2027 የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ COP32ን ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት፣ ከተሞቻችን በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ሰጪ እርምጃዎች ውስጥ ወሳኝ ሚና እንዲኖራቸው እየሰራን ነው ብለዋል ሚኒስትሩ ።
በቤት ግንባታና በከተማ መሠረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም፣ የአካባቢ ዘላቂነትን ማስጠበቅ፣ ሀብትን በቁጠባ መጠቀምና ከአየር ንብረት ጋር ለተያያዙ አደጋዎች ዝግጁ መሆንን ይበልጥ ማበረታታት አለባቸውም ብለዋል ።
ሁሉም የልማት አጋሮች እውቀታቸውን፣ የፋይናንስ ድጋፋቸውን፣ ቴክኖሎጂያቸውንና ተቋማዊ አቅማቸውን ለዚህ የጋራ ሀገራዊ ጥረት የበኩላቸውኝ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል ክቡር ሚኒስትር ኢንጂነር ሙሀመድ አብድራህማን።