ታህሳስ 12, 2025

አለም ገና፣ ህዳር 24/2018 ዓ.ም፣ (ከመልሚ)

የከተማና መሠረተ-ልማት ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ያለፉት 4 ወራት የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ግምገማ እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ልምድም በተሞክሮነት ቀርቧል፡፡

በመድረኩ ላይ የሚኒስቴር መ/ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና የሪፎርም የኮሚቴ አባላት የተገኙ ሲሆን ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተጋበዙ አመራሮችም በስፍራው ተገኝተዋል፡፡

በሪፖርቱ የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የ4 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ስራ እንዲገቡ ከተመረጡት ስምንት ተቋማት መካከል የተሻለ ተሞክሮ እንዳለው የታመነበት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የዝግጅት ምዕራፍ ተሞክሮ ቀርቦ ልምድ እንዲወሰድበት ተደርጓል፡፡

ከዚህም ባለፈ መድረኩ የዘርፉ ተቋማት ወቅታዊ ሁኔታም የእርስ በርስ ልምድ ልውውጥ የተደረገበት ነው፡፡

ስለሪፎርሙ አስፈላጊነት በተሰጠው ገለጻ እስካሁን ባለው ሁኔታ ስብራት ያለበትን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል ፍትሃዊና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን ህብረተሰብ የእርካታ ደረጃ ማሳደግ እንደምገባ በመድረኩ ተገልጿል።

በህዝብ አገልጋይነት ስሜት ሥነ-ምግባርን የተላበሰ ቁመና ያለው ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት
ሪፎርም አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሦስት ዙር ተከፍለው የዝግጅት ምዕራፍ እንዲያከናውኑ ከተለዩት ተቋማት መካከል የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒቴር በሁለተኛው ምድብ ካሉት ስምንት ተቋማት መካከል አንዱ በመሆኑ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በፊት የሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ እንዲያጠናቅቅ የሪፎርም ኮሚቴ ዓባል የሆኑ አመራርና ሠራተኞች በጊዜ የለኝም ስሜት ርብርብ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

Posted in: ዜና