የካቲት 5, 2026

ቢሾፍቱ፣ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) የገጠር መንገድ ትስስርና ተደራሽነት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና የሥነ ምግባርና መከታተያ ስራ አስፈጻሚ በጋራ ፕሮግራሙ የሚያጋጥሙት ብልሹ አሰራሮችን መለየት የሚያስችል ስልጠና የከተማና መሰረተ ሚኒስቴር የዘርፉ ተጠሪ ተቋማት የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች፣ ኃላፊዎች፣ የክልል የፀረ ሙስና ኮሚሽን ተወካዮች እና የክልል የገጠር መንገድ የሥነ ምግባር ፎካል ፐርሰን አካላት ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም በዋናነት በሀገሪቷ የገጠር መንደሮች ከዋና ዋና መንገዶች፣ ከገበያ ማዕከላት እና ከመሰረታዊ አገልግሎቶች ጋር ለማገናኘት የታለመ መጠነ ሰፊ ፕሮግራም የሚከናወንበት እና በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በክልሎች ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ፕሮግራም ነው።

የስልጠናውን መድረክ በንግግር ያስጀመሩት በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የገጠር መንገድ ትስስርና ተደራሽነት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ አሚኒ እንዳሉት ይህ ፕሮግራም በገጠር የሚኖረውን የማህበረሰብ ክፍል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ምርቱን በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲያደርስ የሚያደርግ እና በከተማ የሚኖረውን ህዝብ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ከማድረጉም በላይ በይበልጥ ሴቶችና ህጻናት የህክምና አገልግሎት በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ከፌደራል ጸረ-ሙስና ኮሚሽን የመጡ አቶ አረጎት አብርሃ በዓለም ባንክ ለሚደገፉ ፕሮጀክቶች ከሙስናና ከብልሹ አሰራር የጸዱ ለማድረግ የጋራ ስንምነት መፈራረማቸውን ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ የገጠር ትስስርና ተዳራሽነት ፕሮግራም ማንዋል እና በገጠር መንገድ ፕሮጀክቶች አስተዳደርና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች የሚሉ ሰነዶች ቀርበው የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በማጠቃለያውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባድር ፋሪስ እንደገለጹት ስነ ምግባር መከታታያ መኖሩ ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማስፈን ፕረጀክቱ በአግባቡ ከብልሹ አሰራር ተጠብቆ እንዲሰራና በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጡ ያራሱ የሆነ አስተዋጾ እንደሚበረክት ተናግረዋል፡፡

Posted in: ዜና