ጥቅምት 9, 2025

አድስ አበባ መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የኢት/ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር እየለማ ያለው የግንባታ ቁጥጥርና የመረጃ ስርአት ዝርጋታ ፕሮጀክት በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገምግሟል ፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስተራክሽን ባለስልጣን ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ መረጃ አገልግሎት አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ሀላፊነት ተሰጥቶታል።

ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ወጥነት ያለው፣ ዘመናዊ እና አስተማማኝ የሆነ የመረጃ ስርአትና ተደራሽነትን እውን የሚያደርግ የዲጂታል ሲስተምን ማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ግንቦት 24/2016 ዓ.ም ስምምነት ተካሂዷል።

በስምምነቱ መሰረትም የስራው ሂደት በሁለቱ ተቋማት የቅርብ ግንኙነትና ክትትል ሲደረግበት ቆይቷል። የከተማና መሠረት ልማት ሚኒስቴር እንድሁም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የስራ ሃላፊዎች ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ ከአልሚው ተቋም ጋር በጋራ ግምገማ ተካሂዷል።

ሀገራዊ የንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በማዘመንና በመረጃ በማበልጸግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት የሚታመንበት የተቀናጀ የመረጃ ሲስተሙ ተጠናቆ ለትግበራ ዝግጁ በመሆኑ በቅርቡ ተመርቆ ወደ ሥራ ይገባል፡፡

Posted in: ዜና