የካቲት 5, 2026
አዲስ አበባ፣ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከዘርፉ ተጠሪ ተቋማት ጋር የጀመረውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የስራ ሃላፊዎች ክትትል እና ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አፈጻጸም ሪፖርት እስከ ጥር 3ኛ ሳምንት የተሰሩ ስራዎች ታሳብ በማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሪፎርሙን ጽንሰ ሀሳብ በትክክል በመረዳትና ከዘርፉ ተጠሪ ተቋማት ጋር በተቀናጀና በተናበበ መንገድ፤ ልዩ ትኩረት በመስጠት በዝግጅት ምዕራፍ የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች ተቋማት ማሳያ በሚሆን መልኩ መሰራቱን ለመገንዘብ መቻላቸውን የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ ገልጿል ፡፡
ባለፉት 7 ወራት የተሰሩት ስራዎች የሪፎርሙን ሙሉውን ጽንሰ ሀሳብ ያካተቱ እና በቀጣይ 5 ወራት የተቀሩትን ስራዎች በተጀመረው ፍጥነት እና አረዳድ በማከናወን የዝግጅት ምዕራፉን በተያዘለት ጊዜ በማጠናቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል የቡድኑ አባላት፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር) እንዳሉት ሪፎርሙ ተቋሙ የተቋቋመበትን ዓላማ በትክክል እንዲያሳካ የሚያግዝ በመሆኑ የተሰጡት ግብዓቶች ሁሉንም በሚገባ በመውሰድ ስራችንን በማፋጠን በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን ለማጠናቀቅ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
ከኮሚሽኑ የመጡት የስራ ሃላፊዎች በሪፖርት፣ በሰነድ፣ በሲስተም ከተሰሩት ስራዎች በተጨማሪ ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር አንጻር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰሩ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡