ህዳር 17, 2025
ሰመራ-ሎጊያ ህዳር 06 ቀን 2018(ከመልሚ)
በአፋር ክልላዊ መንግስት ሰመራ ሎጊያ ከተማ የተዘጋጀው የ10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አውደ ርዕይ በይፋ ተከፍቷል።
አውደ ርዕይውን በይፋ የከፈቱት የብልጽግና ፓርቲ ም/ል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ፣ የአፋር ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ክቡር ሀጂ አወል አርባ እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ናቸው።
አውደ ርዕዩ ከተሞች የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር፣ የየአካባቢያቸውን ባህልና ትውፊት ለማሳየት እና የልማትና ኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ ሰፊ እድል እንደሚፈጥር ይታመናል።
“የከተሞች እድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አውደ ርዕይ ላይ ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተውጣጡ ከ150 በላይ ከተሞች እና አስር የተለያዩ የግል ድርጅቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ከተሞች የራሳቸውን ባህል እና የልማት አማራጮች የሚያስተዋውቁበት ኤግዚብሽን እስከ መጪው ህዳር 10 ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።