ጥቅምት 15, 2025
👉🏽በአዲሱ ዓመት መባቻ የበርካታ ዓመታት ቁጭታችን እና የጥረታችን ውጤት የሆነውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ያስመረቅንበት፤
👉🏽በወርሃ መስከረም መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ሀብት የብስራት ጅማሮ የሆነውን የተፈጥሮ ጋዝ ያወጣንበት
👉🏽የተፈጥሮ ሃብታችንን በመጠቀም የዕድገታችን መልህቅ የሆኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የጀመርንበት ነው።
👉🏽ይህም በመሆኑ ይህ ዘመን በታሪካችን ውስጥ በጉልህ የሚወሳ አዲስ ምዕራፍ ሊሆን እንደሚችል አልጠራጠርም።
👉🏽የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም ቀደም ሲል በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ ተይዘው በተከታታይ ዓመታት ተግባራዊ ሲደረጉ በቆዩ ፕሮግራሞች ኢኮኖሚያችን በማንሰራራት ላይ ይገኛል።
👉🏽የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለዘመናት በመዋቅራዊ ተግዳሮቶች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ይገኝ ነበር።
👉🏽ከለውጡ በፊት ይመዘገብ የነበረው ዕድገትም በዘላቂ የፋይናንስ መሠረት ላይ ያልተዋቀረ፤ ሀገርን ለከፍተኛ ዕዳ የዳረገ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን የፈጠረ ነበር።
👉🏽መንግሥት እነዚህን የኢኮኖሚ መዛባቶች የሚያርሙ እና ወደ ብልጽግና ጎዳና የሚያደርሱ ፈጣን እና መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተግባራዊ አድርጓል።
👉🏽የመንግሥት ገቢ፣ የወጭ ንግድ (ኤክስፖርት) እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ለማሳደግ ተችሏል።
👉🏽የልማት አቅጣጫችን ትኩረትም ውስን ከሆኑ ዘርፎች ወደ ባለብዙ የኢኮኖሚ መሠረቶች መቀየር ላይ ይገኛል።
👉🏽 መንግሥት ኢኮኖሚውን ከዕዳ ጥገኝነት በማላቀቅ ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ለማሸጋገር የሚያስችል ወሳኝ ምዕራፍ ከፍቷል።
👉🏽 የኢኮኖሚ ለውጡ መሠረቶችም ያሉንን አቅሞች ማወቅ፣ በችግር ውስጥ ዕድሎችን ማየት፣ በፈጠራ እና በፍጥነት፣ በትብብር እና የተለያዩ አቅሞችን በማሰባሰብ እንዲሁም ዘላቂ ግቦችን በማሳካት ላይ ያተኮሩ ናቸው። እነዚህ መሠረቶች አጠቃላይ ሀገራዊ ዕድገትን ለማፋጠን አስችለዋል።
👉🏽 በዚህም ከዕዳ ጫና በመላቀቅ፣ በራስ አቅም ችግሮችን በመፍታት፣ ከአግላይ የኢኮኖሚ ሥርዓት ወደ አሳታፊ እና ምቹ የኢኮኖሚ ምሕዳር በመሸጋገር ከዝናብ ጥገኝነት ወደ ራስ ቻይ አምራችነት በመብቃት የማዕድን ጥሪታችንን ወደ ወሳኝ የሀብት ምንጭነት በመቀየር፣ የቱሪዝም ሀብታችንን ከመዳህ ጉዞ ወደ ጉልህ የዕድገት አንቀሳቃሽነት በማሳደግ የሕዝባችንን አኗኗር ለመለወጥ እና ዘላቂ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።
👉🏽 በዚህ መሠረት የሀገራችን ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት 8.8 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል።
👉🏽 በግብርና በ2016 በጀት ዓመት 1.2 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ተመርቶ የነበረ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት 1.57 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ተመርቷል።