ሐምሌ 7, 2025

በበጃት ዓመቱ ውጤት የተገኘባቸው ክንውኖችና በቀጣይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ተነስተው በዕለቱ ሰፊ ግምገማ ተካሄዷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ/ም (ከመልሚ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ላይ የተጉኙ ውጤቶች የዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም እንዲሁም የዘርፉ ዋና መሪ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሄዷል፡፡

በበጃት ዓመቱ ውጤት የተገኝባቸው ዋና ዋና የተግባራት ክንውን የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት፣ የከተሞች ሴፍቲኔትና ምግብ ዋስትና ማስፋፋትና ማሳደግ ስራዎች፣ የከተማ ፕላንና የትግበራ ኦዲት ማጠናከር ስራዎች፣ የከተማ መሬት አስተዳደርና የካዳስተር ስርዓት ዝርጋታ ስራዎች ክንውንና የ2018 በጀት ዓመት የዘርፉ ዋና መሪ ዕቅድ በሚኔስቴር ደኤታው አማካሪ አቶ ሀብታሙ መውደድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን በዘርፉ እየተተገቡሩ ያሉ ዓበይት ተግባራት አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ መሻሻሎች እየታዩባቸው ያሉ አመረቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን ገልጸው፤ ለዓብነትም የከተሞች ማዘጋጃ ቤታዊ ስርዓት እያደገና እየተሸሻለ መምጣት፣ አብዛኛው ከተሞች ገቢያቸውን መሸፈን የሚያስችላቸው ደረጃ ላይ መድረስ፣ የከተሞች ልማታዊ ሰፍትኔት ፕሮግራም በምሳሌነት መጥቀስ የሚስችል ተግባር መከወኑን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ሚኒስቴር ዴኤታው መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች አንስተው በቀጣይ በጃት ዓመት ድክመት የታየባቸው ተግባራት ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ላይ አመላክተዋል፡፡

ሪፖርተር ኮከቤ ቢፍቱ
የካሜራ ባለሙያ ፈዬ ደሜ

Posted in: ዜና