 
			ጥቅምት 10, 2025
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከሪልስቴት አልሚዎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባካሄደው የጋራ ውይይት የቤት ልማት ፕሮግራም ከተለመደው ኋላ ቀር አሠራር በመውጣት ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደምገባ ተመላክቷል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በውይይቱ እንዳሉት ከተለመደው ኋላ ቀር አሰራር በመላቀቅ ዘመኑ የሚፈልገውን የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂን መጠቀም የህዝባችንን የቤት ፍላጎት በአግባባ እና በፊጥነት መመለስ አለብን ብለዋል።
የቤት ልማት ችግርን ለመፍታት በዋናነት የቤት አሰራር ስርዓት ዝርጋታ ላይ ያለው ልምድ ግልጽነትና መተማመን በተሞላበት እንዲሁም ከግል ፋላጎት ይልቅ ለሀገር ለውጥ ማሰብ ያስፈልጋል በማለት በኮሪደር ልማቱ የመጣው ለውጥ እንደተሞክሮ መስደን ለቤት ግንባታ ብናውለው አመርቂ ውጤት ማምጣት ይቻላል በሚል ክብርት ሚኒስትሯ አክለው ተናግረዋል፡፡
በውይይቱም የተሳተፉት አካላት የተለያዩ ተሞክሮዎች እና ሀሳቦች አንስተው የተሻለ የሚሆነው ለሀገር ለውጥ እና እድገት እስከሆነ ድረስ ሁላችንም አንድ በመሆን የመንግስትን አቅድ ለማሳካት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል፡
 
			