የካቲት 24, 2026
አዳማ፣ የካቲት 17/2018 ዓ.ም፣ (ከመልሚ)
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት እና ስራ ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ግምገማና የ3ኛ ዙር ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ ማብሰሪያ መድረክ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ነው፡፡
በዓለም ታሪክ በተረጅነት የበለጸገ ሀገር እንደሌለ የገለጹት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ልዩነቱ የተገኙ ዕርዳታዎችን ተጠቅሞ ለውጥ ለማምጣት ጥረት ማድረግ ሲቻል ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እስካሁን በተሰሩ ስራዎች በፕሮግራሙ የታቀፉ ተጠቃሚዎች ባገኙት ስልጠና እና በተሰጧቸው የስራ ላይ ስምሪቶች በጽዳትና ውበት፣ በአነስተኛ መሠረተ-ልማት፣ ወዘተ. ስራዎች ላይ በመሰማራት የተገኙ ውጤቶች በአርዓያነት የሚጠቀሱ በመሆናቸው ይሄንኑ አጠናክሮ በማስቀጠል እንዲሁም በእጥረት የተነሱ ጉዳዮችን በማሻሻልና የተሰጡ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ወስዶ በመተግበር ባጠረ ጊዜ ከተረጂነት ወደ አምራችነት መሸጋገር ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በተሰሩ ውጤታማ ስራዎች የተገኙ ውጤቶች በ3ኛ ወገን ተቀባይነት በማግኘታቸው ተጨማሪ ድጋፍ ማግኘት እንደተቻለና ከዓለም ባንክ በተገኘው የ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የተጠቃሚዎች ልየታ መስፈርቱን የተከተለና ስነ ምግባርን በተላበሰ መንገድ በጠንካራ ዲሲፕሊን ሊመራ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡
የእርሳቸውን የመክፈቻ ንግግር ተከትሎ በመድረኩ ላይ የ3ኛው ዙር ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እና የዋና ኦዲተር ክዋኔ ኦዲት ግኝት ሪፖርት እንዲሁም የዓለም ባንክ ገለልተኛ የግዢ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ በቀረቡት ሠነዶች ላይ የጋራ ውይይት ተደርጓል፡፡
በቀጣይም በፕሮጀክቱ የምልመላና የቅሬታ አፈታት ሥራዎች ላይ ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ ሂደቶችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሠነድ ቀርቦ የጋራ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን ይህን ተከትሎም በፕሮግራሙ የታቀፉ ከተሞች የመስክ ክትትልና ድጋፍ ግኝት ሪፖርቶች ቀርበው የጋራ ውይይትና ማጠቃለያ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡