የካቲት 24, 2026
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒሰቴር የዘርፉ የተጠሪ ተቋማት(የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት) የ2018 በጀት ዓመት የ7 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄዷል።
ከ3ቱም ተጠሪ ተቋማት በቀረቡት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንደየ የስራ ባህሪያቸው በዝርዝር አቅርበው የጋራ ውይይት ተካሄዷል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር) እንዳሉት ከሶስቱም ተጠሪ ተቋማት የቀረቡት የእቅድ አፈጻጸም አበረታች እንደሆኑና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ መጠናቀቅ፣ የኮንስትራክሽን ግንባታ ግብአቶችን ጥራትና አጠቃቀም በአግባቡ ከመለየት አንጻር፣ ከበጀት አጠቃቀም አንጻር፣ ከግዥ ስርዓትን አንጻር በአግባቡ መሰራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በቀጣይም ፕሮጀክቶች በእቅዱ መሰረት ከክልሎች ጋር በመናበብ ለላቀ አፈጻጸም መትጋት፤ መሶብ(የአንድ ማዕከል አገልግሎት)ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት እንዲሁም ለሪፎርም ሥራ መፋጠን ሚኒሰቴር መሥሪያ ቤቱ እና የዘርፉ ተጠሪ ተቋማት ተግቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትር ደኤታው የሥራ መመሪያ እና አቅጣጫ ሰጥተዋል።