ነሐሴ 1, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ/ም (ከመልሚ) የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት፣ በቦሌ አካባቢ እየተገነቡ የሚገኙት የቢሮ ህንጻዎች ሎት አንድ እና ሎት ሁለት ለኢትዮጵያ ሜትሪዎሎጂ ኢንስቲትዩት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን ህንጻ ፕሮጀክት አፈጻጸምን የተመለከተ የመስክ ምልከታ አካሄደዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በሳንታማሪያ ህንጻ ተቋራጭ እና በይርጋለም ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር አማካኝነት እየተገነቡ የሚገኙ ሲሆን ከተቋራጭ ድርጅቶች ጋር በተገባው ውል መሠረት የግንባታ ሂደቱ በቅርብ ቀን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል ፡፡

ሪፖርተር: ኮከቤ ቢፍቱ
ፎቶግራፍ :አስመላሽ ተፈራ

Posted in: ዜና