ህዳር 26, 2026
ኢትዮጵያ በ2030 የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን በምታደርገው የልማት ጉዞ የመንገድ ዘርፉ በአገሪቱ የሚከናወኑ ምጣኔ ሃብት እና ማህበራዊ እድገት ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑ የሚታመን ነው፡፡
ይህን በመገንዘብ፣ መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የምጣኔ ሃብት እና ማህበራዊ ዕድገት ዘላቂነት እና ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ አዲሱ የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም የገጠሩን ማህበረሰብ ትስስርና ለተለያዩ መሰረታዊ አገልግሎቶች ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ በቀበሌ ደረጃ ያሉ መንደሮችን እና በአርብቶ አደር አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦችንም ተደራሽ በሚያደርግ መልኩ በፕሮግራሙ ውጤታማ ስራዎችን ተሰርቷል፡፡
የገጠሩን ማህበረሰብ እርስ በርስ እና ከማእከላት ጋር በማስተሳሰር እና ተነጥለው ያሉ አካባቢዎችን በማገናኘት እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የገጠሩን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል እና ለምግብ ገበያ እና ለተለያዩ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ማሳደግ ነው።
ፕሮግራሙ በ12 ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባሉ 126 ወረዳዎች እየተተገበረ ይገኛል፡፡
ኖቬምበር 18/2026 በጄኔቫ በተካሄደው የIRF(International Road Federation) 2026 ዓመታዊ ጉባኤ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የገጠር ትስስር እና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድአምን አደም ሽልማቱን ተቀብለዋል።