ነሐሴ 17, 2026
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 30 ቀን፣2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) ተቋማቱ የተወያዩት የስፓሻል መረጃ መጋራት፣ የደህንነት ምደባ እና በተቋማት መካከል ትብብርን የሚያጠናክሩ ተቋማዊ ማዕቀፎች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ነው።
የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በውይይት እንደተናገሩት በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች ትክክለኛ የመሬት መረጃን በአግባቡ በመሰብሰብ ቆጥሮ መያዝ ከተቻለ ከተሞች ለዜጎቻቸው ግልጽ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ከተሞች የተሻለ ገቢ በመሰብሰብ እድገታቸውን ማፋጠን እንደሚችሉ አብራርተዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም የድሮን ቴክኖሎጂን መጠቀም ለፖሊሲ ዝግጅት፣ አጠቃላይ የከተማ ዋና ሀብት የሆነውን መሬት ለማስተዳደር፣ ለውሳኔ አሠጣት፣ የድጅታላይዝ አሠራርን ተግባራዊ ለማድረግ፣ ለኮሪደር ልማት እንዲሁም ለአጠቃላይ የመሠረተ-ልማት ሥራዎችን ለማፋጠንና ለመከታተል ሁነኛ መፍቴሔ በመሆኑ ከተቋሙ ጋር በጋራ ለመስራት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ነን ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢንፎርሜሽኝ መረብ ደህንነት አገልግሎት(INSA)ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትእግስት ሀሚድ እንደተናገሩት በድሮን ቴክኒዎሎጂ የታገዘ የአየር ፎቶ 3D ሞደል የካዳስተር ስርዓትን ከ2ዲ ወደ 3ዲ በመቀየር በከተሞች የፕላን ጥሰትን ለመከላከል፣ የመሬት ሀብት አጠቃቀምን ሥርዓት ከማስያዙም በላይ ለሀገር ዕድገት፣ ለሀይል አቅርቦት ተደራሽነቱ ለኢኮኖሚ፣ ለእውቀት ሽግግር እና ለስማርት ሲቲ(ስሉጥ ከተማነት) ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የከተማ መሬት መረጃዎችን በተደራጀና በተናበበ መንገድ የሚያዝበት እንዲሁም ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት ያለ ብክነት ከተዝረከረከው አሰራር ለመጠበቅ በዲሮን ቴክኖሎጂ የአየር ፎቶ 3D ምደል ፕሮጀክት፣ ብሔራዊ የቁጥጥር መስፈርቶችን ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችሉ ገዳዮች በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ የባለሙያ ምክሬ ሀሳቦች በመድረኩ ቀርበዋል።
በዋናነት በአዳማ ከተማ የተጀመረውን 2D/3D ካርታ ሥራ ሞዴልን ወደ ሌሎች የሀገራችን ከተሞች ማስፋፋት በሚቻልበት ሁነታ ላይ ውይይት ተደርጓል በቀጣይ በነዝህ እና መሠል ጉዳዮች ተቋማቱ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።