መስከረም 9, 2026

አዳማ፣ ነሐሴ 30 ቀን፣2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) የግንዛቤ ማስቸበጫ ስልጠና የታለመለትን ግብ እዉን ለማድረግ በሁሉም ስራ ክፍሎች በ2019 በጀት ዓመት ጊዥዎች በመመሪያው ብቻ እንዲከናወን ተገልጿል።

በስልጠናው ላይ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበራ አመንታ እንደተናገሩት ሁሉም ስራ ክፍሎች  የግዥ ዕቀድን ሲያቅዱ ሁሉንም የህግ ማዕቀፎችን ጠንቅቀው በማወቅ በጀትን በጊዜ፣ በዋጋ፣ በጥራት እና በጥንቃቄ እንዲሁም በተጠያቂነት ማዘጋጀት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የዕለቱን የግዥ አጠቃላይ የህግ ማዕቀፎችን አስመልክተው ስልጠና የሰጡት የፌደራል መንግሰት የግዥና ንብረት ባለስልጣን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዳብራሩት ተቋማት ከዘልማዳዊ የግዥ ስርዓት ወጥተው መንግስት በሚፈለረገውና በዘረጋው የድጅታል አሰራርን ተከትለው መሄድ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተው፡፡

በአሁኑ ወቅት በሁሉም ፌደራል ተቋማት ግዥ መፈጸም ያለበት በኤሌክትሮን ግዥ መሆኑን ጠቅሰው በተለያዩ ምክንቶች የተቋም የበላይ አመራር ከፈቀደ ብቻ መካናወን እንደሚቻል ለሰልጣኞች አብራተዋል፡፡

የስልጠና ተሳታፊዎች በአተገባበር ወቀት የሚጋጥማቸውን ተግዳሮት ለአስልታኞች በጠየቁት መሠረት ተገቢው ምላሽ ማብራሪያ ተሰጥቶቸዋል፡፡

Posted in: ዜና