ግንቦት 22, 2026
አዳማ፣ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም. (ከመልሚ)
ይህ የተገለጸው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የሥራ ፕሮጀክት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዳማ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡
የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የሥራ ፕሮጀክት ድህነት ላይ አተኩሮ በመስራት ለዝቅተኛ ነዋሪዎች የስራ ዕድልን የፈጠረና ዜጎች ከተረጂነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ በሀብታምና በደሃ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብና ዜጎች ወደ ሀብት ጉዞ እንዲያመሩ በማድረግ በአፍሪካ ደረጃ ሞዴል መሆን የቻለ፤ በዓለም ባንክና በሌሎች የልማት አጋር ድርጅቶች ዕውቅና የተሰጠው ውጤታማ ፕሮጀክት ነው ብለዋል ሚኒስትር ድኤታው፡፡
በውይይት መድረኩ በሦስተኛው ሩብ ዓመት በ21 ከተሞች በተደረገ የመስክ ክትትልና ድጋፍ በተገኙ ግኝቶች ላይ የጋራ ውይይት ተደርጓል።በማጠቃለያ ላይ ካለፉት ዓመታት መሻሻሎች እንዳሉ ተገልጾ በቀጣይ ይበልጥ መሻሻል ባለባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 11 ክፍለ-ከተሞችን ጨምሮ በሌሎች 32 ከተሞች ላይ በገለልተኛ አካል በተጠና የፕሮጀክት ግዥ የኦዲት ግኝት ጥናት ላይ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ በተሰጠ ማጠቃለያ ላይ ከቀረቡ ምክረ-ሀሳቦች መካከል በዋናነት፡- የግዥ መዘግየትን መቀነስ፤ በጀትና ዕቅድን ማጣጣም፤ ቴክኒካል ግምገማን ማካሄድ፤ የሠነድ አያያዝን ማሻሻል፤ የርክክብና የፍተሻ ሠነዶችን መዝግቦ መያዝ፤ አቅርቦትና ክፍያን ፈጥኖ ማጠናቀቅ፤ የገበያ ጥናትና የዋጋ ግምትን ማጣጣም የሚሉና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ምክረ-ሀሳቦች ያቀርበዋል።
ጥናቱ በተካሄደባቸው ከተሞች ውስጥ ያሉ የፕሮጀክት አስፈጻሚዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የተሻሻለ ሪፖርታቸውን ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር አጣጥመው እለመላክ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን በተደረገው የኦዲት አጠቃላይ ግምገማ የግዥ ሂደቱ በአብዛኛው የዓለም ባንክ መስፈርትን አሟልቶ የተከናወነ መሆኑንና መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
በተሳታፊዎች በኩልም በተሰጠው አስተያየት መሠረት የተገኘ ሀብትን በአግባቡ ከማስተዳደርና ጥቅም ላይ ከማዋል አንጻር የተፈጠሩ የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመሙላት መድረኩ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን በሰጡት ቀጣይ አቅጣጫና የሥራ መመሪያ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የቀረቡ ሰነዶችና የተነሱ ሃሳቦች እንዲሁም የተደረጉ የጋራ ውይይቶች ጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው በአጠቃላይ መድረኩ የተሻሉ ተሞክሮዎች የታዩበት፣ የተፈጠሩ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችል ግንዛቤ የተፈጠረበት እንደነበር በማስታወስ በተሰራው ስራና በተገኘው ውጤት መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ሊተኮርባቸው ይገባል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
የዜጎችን ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና የተመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠል እንዲሁም የተገኘውን ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ በአግባቡ ለማስተዳደርና ለመምራት የተጠቃሚዎችን ምልመላ በጥራት በመስራት ስራዎችን ከአካባቢ ልማት ጋር የተስማሙ እንዲሆኑ ማድረግ፤ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል፤ የኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፤ ከዕቅድ እስከ አፈጻጸም በሚሰሩ የኦዲት ስራዎች ላይ የክትትልና ግምገማ ስርዓትን አጠናክሮ ማስቀጠል፤ የፋይናንስ አስተዳደርና የግዥ ስርዓትን በአግባቡ መምራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡