መጋቢት 25, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የፕሮጃክት አፈጻጸም በየጊዜው በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ገልጸው ለዓብነትም በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟሉ ፕሮጀክቶች ተሰርተው በመጠናቀቃቸው የሚታይ ለውጥ ማምጣት መቻሉኑን ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ የፕሮጃክት አስተዳደር በኢትዮጵያ (PMI Ethiopia Chapter) እንዲሁም በ2026 በተመሳሳይ ከአፍሪካ ከተወከሉ ተቋማት ጋር በተጠናከረ መልኩ አብሮ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

የስምምነት ሰነዱ (MOU) በዋናነት በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋና ዋና ሁነቶችን በጋራ ማዘጋጀት፣ ሁለቱ ተቋማት ተደራሽነታቸውን በተለያዩ ሴክተር ተቋማት ላይ ማስፋት፣ በሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዞ መስራት ላይ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት (CMI) እና ዓለም አቀፍ የፕሮጀክት አስተዳደር በኢትዮጵያ (PMI Ethiopia Chapter) በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት  ሰነድ ተፈራርመዋል።

ተቋማቱ የተፈራረሙት የስምምነት ሰነድ የስልጠናና የልምድ፣ የዕውቀትና የትብብር ስራዎችን በቅንጅት በመስራት በቀጣይ ሀገራዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል፡፡

በ2026 በአለም አቀፍ ፕሮጀክት አስተዳደር የተወከሉ የየቻርተሩ ፕሬዝዳንቶች አዲስ አበባ ከተማን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት እጅግ የሚያስደስት እና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት የሆኑ ስራዎች እንደተሰሩ እና ከተማዋን በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

Posted in: ዜና