ህዳር 4, 2025
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የዩጋንዳ የመሬት ኮሚሽን ልዑካን ቡድን ከከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር አጠቃላይ ስለሀገሪቱ የከተማ መሬት አስተተዳደር በተመለከተ የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሬት አስተዳደርና ካዳስትር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙዓለም አድማሱ አጠቃላይ የሀገሪቱን መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስለ ህብረተሰቡ አኗኗር እና የሀብረተሰቡን እሴቶችን እንዲሁም ስለ ከተማ መሬት አስተዳደር ከቀደመው ኋላ ቀር አሰራር አሁን ላይ የድጅታላይዘሽን አሠራር ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር በዝርዝር ለልዑካን ቡድን አቅርበዋል፡፡
ይህን ተከትሎ የዩጋንዳ የመሬት ከሚሽን በየደረጃው የሚገኙ ልዑካን ቡድን አባላት በኢትዮጵያ በከተሞች ስለ መሬት አስተዳደር፣ ካዳስተር፣ የከተማ ገቢ አሰባሰብ፣ ስለ ድጅታላይዘሽን፣ ስለካሳ አከፋፈል እና ሀገሪቱ ስላላት የመሬት ፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን አስመልክተው የተለያዩ ጥያቄዎችን በዝርዝር አንስተዋል፡፡
እንደ ሀገር መሬት የመንግስትና የህዝብ መሆኑን እና በተዋረድ በየክልሉ የሚገኙ መንግስታት መሬትን በጨረታ፣ በምደባ ሲሰጡ እንደሚችሉ በውይይቱ ለልዑካኑ ገለጻ ተደርጓል ፡፡
በመጨረሻም ልዑካን ቡድኑ ስልከተማ መሬት ከፖሊሲ እስከ አተገባበር ድረስ በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል በተሰጣቸው ገለጻና ማብራሪያ መሠረት ግንዛቤና ተሞክሮ ማገኘታቸውን ገልጸው ከኢትዮጵያ መልካም ተሞክሮ እንዳገኙ ተናግረዋል ፡፡
የልዑካን ቡድኑ በቀጣይ በአዲስ አበባ ከተማ ድጅታላይዘሽን አተገባበር እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጉብኝት ያደርጋሉ ፡፡