ታህሳስ 31, 2025

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና የፍትህ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሀና አርዐያስላሴ እንዲሁም ክቡር የትምጌታ አስራትን(ዶ/ር) ጨምሮ የፕሮጀክቱ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሜክሲኮ ተግባረእድ አካባቢ 22 ወለል ከፍታ ያለው የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና መስሪያቤት ህንጻ ግንባታ ያለበት የአፈጻጸም ደረጃ ተጎበኘ፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በፌደራል መንግስት ህንጻዎች ግንበታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ስራ ተቋራጭነት በመከወን ላይ ያለው የህንጻ ግንባታ በቀጣይ 88 የግንባታ ቀናት ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል፡፡

Posted in: ዜና