October 20, 2024

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሬትና ካዳስተር መሪ ስራ አስፈፃሚ ከማእከላዊ ኢትዮጲያ፣ ከኦሮምያ፣ ከደቡብ አትዮጲያ እና ከሲዳማ ክልሎች ለተወጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች በመሬትና ካዳስተር ዘርፍ ባሉ የህግ ማዕቀፎችና የአሰራር ስርዓቶች ላይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የስልጠናውን መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ዘርፉ ዘውዱ እንዳሉት የከተማ መሬት ከሌብነት እና ከብልሹ አሰራር ለመታደግ የመሬት ሀብታችን ቆጥሮና መዝግቦ በመያዝ የነዋሪዎችን ፍላጎት ማሟላት እንደምገባ ገልጸዋል ።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በመሬትና ካዳስተር መሪ ስራ አስፈፃሚ የልማት ተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ዴስክ ሃላፊ አቶ ሀይለማርያም ወርቃለማው የተሻሻለው የካሳ አዋጅ 1336/2016 ሰነድ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ለተለያዩ ዓላማዎች መሬት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በልማት የሚነሱ አካላት በአግባቡ መልሶ ማቋቋም ያስፈልጋል ብለዋል።

በስልጠናው የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

Posted in: News Uncategorized