July 14, 2025

ይህንን መሰረት በማድረግ  የዘርፍ ተኮር የአሰራር ስርዓት ጥናት ከኢንቨስትመንት መሬት አቅርቦት እና ከመንገድ አሰራር ጋር በተያያዘ የተጠኑ ጥናቶች አስመልክቶ  የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የፀረ ሙስና ኮሚሽን የበላይ አመራሮች በተገኙበት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የጋራ ውይይት ተካሄዷል፡፡

በመድረኩም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ካጠናቸው ጥናቶች መካከል በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ፣ በመሬት አጠቃቀም እና ህዝቡን የሚያግዙ መሰል ዘርፎች ላይ የተጠኑ ጥናቶች በዋናነት የሚጠቀሱ በመሆኑ እና ይሄንን የሚያስፈልግበት እና የሚያስገድድበት ጊዜ ላይ ስለሆንን ጥናቱ ጠቃሚ ነው በማለት ገልጸው፤ የጥናቱን ውጤት በቀጣይ በ2018 በጀት አመት በማካተት ተግባራዊ የምናደርገው ይሆናል ብለዋል፡፡ 

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ም/ዋ/ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው እንዳሉት ጥናቱ ከአዲስ አበባ፣ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልሎች ጋር በጋራ በመሆን የተጠና ጥናት እንደሆነ በመጥቀስ  አብዛኞቹ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጥናቱን መሰረት በማድረግ እቅድ አቅደው ወደ ስራ እየገቡ እንደሆነና ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ከመሬት አቅርቦትና ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ጋር ተያይዞ ብልሹ አሰራሮች እንዳሉም  ተናግረዋል፡፡

በመድረኩም ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ስር የኢንቨስትመንት መሬት አቅርቦትና የአሰራር ስርዓት እንዲሁም በኮንስትራክሽን ዘርፉ የመንገድ ስራን አስመልክቶ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት የአሰራር ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በዘረፉ ላይ የሚሰሩ አካላት በመቀራረብና በመግባባት ስራን በመስራት ብልሹ አሰራርን መከላከል ያስፈልጋል የሚልና መሰል ምክረ ሀሳቦችን በስፋት ተነስተዋል፡፡

ይህንን መሰረት በማድረግ ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው በክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች እና  በክቡር ምክትል ኮሚሽነር የማጠቃለያ ሀሳብ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ሪፖርተር ኮከቤ ቢፍቱ
የካሜራ ባለሙያ ፈዬ ደሜ

Posted in: News