
October 20, 2024
ቀደም ሲል በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የመሠረተ-ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትና በቅርቡ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው የተሸሙት ክቡር ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በትናንትናው ዕለት ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
በሽኝት መርሃ-ግብሩ ላይ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒና ክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ስለነበራቸው መልካም የሥራ ግንኙነት እና በጋራ ስላከናወኗቸው መልካም ተግባራት ያላቸውን አክብሮትና አድናቆት ገልጸው በሄዱበት ቦታም እዚህ የነበራቸውን የስራ ትጋት፣ አብሮ የመስራትና ለውጤታማነት የመብቃት ጥረታቸውን አጠናክረው በመቀጠል ለስኬት እንዲበቁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡
ክቡር ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) በበኩላቸው ስለተደረገላቸው አሸኛኘትና በስራ ሂደት ስለነበራቸው መልካም የስራ ግንኙነት ከአጋሮቻቸው ለተሰጣቸው አድናቆትና መልካም ምኞት ምስጋናቸውን አቅርበው በሄዱበት ቦታም የሚሰሩት የከተማና መሠረተ-ልማት ስራን በመሆኑ አብሮነታቸው እንደማይለያቸውና ድጋፋቸውን እንደሚሹ ገልጸዋል፡፡


















