
June 11, 2025
ጅማ፣ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ/ም(ከመልሚ)
ይህ የተገለፀው በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አዘጋጅነት ለኦሮሚያ ክልል በክልል እና በከተማ ደረጃ በቤቶች ዘርፍ ለሚሰሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች በጅማ ከተማ በተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ነው።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 እንዲሁም በሪል እስቴት እና በቋሚ ንብረት ግመታ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
የስልጠናው መድረክ በንግግር ያስጀመሩት በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ትግስት አለሙ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት የተለያዩ አዋጆች፣ደንቦች፣ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎች ከማውጣት ጋር ተያይዞ በክልሎች እና በከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በአሁን ጊዜ በከተሞች የህዝብ ጥቁር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመሩ ምክንያት በከተሞች የሚስተዋለው የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት መንግስትና የግሉ ዘርፍ በትኩረት መስራታቸውን ገልጸው ይህንንም ተግባራዊ እንዲሆን በዘርፉ ያሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ በማለት ስራ አስፈፃሚዋ አያይዘው ተናግረዋል።
በመድረኩ የ10 አመት የቤት የልማት ዘርፍ መሪ እቅድ ፣በሪል እስቴት አዋጅ እና ረቂቅ ደንብ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 እንዲሁም በክልሉ ከተሞች በመኖሪያ ቤት ልማት፣ በማስተላለፍ እና በመልሶ ማልማት የተሰሩ ስራዎች በኦሮሚያ ክልል የከተማ ተወካዮች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ በቀጣይ መሰራት የሚገባቸው ስራዎች በመለየት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
ሪፖርተር ኮከቤ ቢፍቱ
የካሜራ ባለሙያ ፈዬ ደሜ