March 17, 2025

አዳማ፣ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ/ም (ከመልሚ)

በከተማ ፕላንና አከታተም፣ በከተማ መሬትና ካዳስተር፣ በማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ማዘመን እና በማዘጋጃቤታዊ ገቢዎች ዙሪያ ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄዷል ።

በልምድ ልውውጥ መድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራር አካላት፣ የከተማ ከንቲባዎች፣ የዘርፉ የክልል የቢሮ ሃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በልምድ ልውውጥ መድረኩ እንደገለጹት መንግስት ለከተሞች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ሲሆን ከተሞች የለውጥ ፣ የእድገት እና የብልጽግና ማእከል ለመሆን የበኩላቸውን ሚና ልወጡ ይገባል ብለዋል።

ከተሞች ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን እና ዲጂታላይዝ ከማድረግ አንጻር ፣ የማዘጋጃ ቤታዊ ገብን ከማሳደግ እና ስማርት ከተማን ከመገንባት ረገድ በትኩረት መሰራት እዳለበት ገልጸዋል።

በልምድ ልውውጡ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የከተማው አመራር በትኩረት በመከታተል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት መሬት ላይ አውርደው ተግባራዊ እንዲያደርጉ በአጽንኦት ተናግረዋል ።
የአዳማ ከተማ ከነበረችበት ውስብስብ ችግር በመውጣት አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ በመድረሷ እና በተለይም ስማርት አዳማን አውን በማድረግ ረገድ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጅታላይዝ በማድረግ ከንክክ የጸዳ እንድሆን፣ የከተማውን የመሬት ሀብት በካዳስተር ስርአት ሙሉ በሙሉ በመመዝገብ እና ብልሹ አሠራርን በመግታት ለሌሎች የሀገራችን ከተሞች መልካም ተሞክሮ መቅሰሚያ ከተማ ነች ከተሞቻችንም የተሻለ ልምድ ቀስመው ወደ ከተሞቻቸው ነባራዊ ሁነታ በመቀየር ከተሞቻቸውን ሊያበለፅጉ ይገባል ብለዋል ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ።

የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጃልዴ በበኩላቸው በአዳማ ከተማ በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸው በተለይ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ፣ የከተማዋን ኢንቨስትመንት አማራጭ ከማስፋት፣ አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን እና ህዝብና መንግስት ከማገናኘት ጋር ተያይዞ በረካታ ስራዎች መሰራታቸውን   አብራርተዋል።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ያሰራው የከተማ አስተዳደሪ ህንጻ ግንባታ  የተጎበኙ ሲሆን የአዳማ ከተማ ተሞክሮ ለሌሎች ከተሞች ተምሳሌት እንደሚሆን ተገልጿል።

በልምድ ልውውጡ ላይ የተሳተፉት የክልል የስራ ሀላፊዎች እና ከንቲባዎች በሰጡት አስተያየት በአዳማ ከተማ በተሠሩት ስራዎች ከፍተኛ ልምድ መቅሰማቸውን እና ለሌሎች የሀገራችን ከተሞች ሮል ሞደል መሆን የሚችል ስራ መሆኑን ገልጸዋል ።

ሪፖርተር:- ኮከቤ ቢፍቱ
የካሜራ ባለሙያ:- ድንቅነሽ ኤርቃሎ

Posted in: News