
December 30, 2024
አዳማ ፣ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም (ከመልሚ)
የሁሉም ክልል እና የከተማ አስተዳደር የዘርፉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና የሚዲያ አካላት የተሳተፉበት የጋራ ፎረም በአዳማ ከተማ ተካሄዷል ፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ኢትዮጵያ በደቻ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው እንደተናገሩት ይህ የህዝብ ግንኙነት ፎረም በለፉት አመታት ስራዎችን በተሳለጠ እና ግንኙነትን በሚያጠናክር መልኩ በርካታ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘርፉን ታሳቢ ያደረጉ የተለያዩ ፖሊሲዎች እና የህግ ማእቀፎች በማዘጋጀት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጸድቀው የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ ሆነው ነገር ግን በተፈለገው አግባብ በህዝብ ግኑኝነት እና የሚዲያ አካላት ህብረተሱቡን ግንዛቤ ማስጨበጥ ካልተቻለ የህብረተሰቡን ጥያቀና እሮሮ ያባብሳሉ የዝህ መድረክ መዘጋጀት አላማም ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ታሳብ ያደረገ ነው ብለዋል አቶ ኢትዮጵያ።
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክብርት ሚኒስትር አማካሪ አቶ ደጀን እሸቱ እንዳሉት የህዝብ ግንኙነት መዋቅር እንደ ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው በተገቢው መንገድም እየተመራ እንደሆም ገልጸዋል።
የህዝብ ግንኙነት ስራ ወቅቱን ከሚጠይቀው አንጻር በቴክኖሎጂ ተደግፎ የሚሰራ ሲሆን የሚቀርቡት ሰነዶች በትኩረት በመከታተል ያገኛችሁትን እውቀት ለህዝባችን ተደራሽ ማድረግ ይኖርባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።
በእለቱ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህንፃና ሌሎች ግንባታዎች ክትትልና ቁጥጥር ዴስክ ሃላፊ አቶ ካሳ ከበደ የተሻሻለው የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ ሲያቀርቡ እንዳሉት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ለሚያጋጥሙ ክፍተቶች መፍትሔ የሚሆን አዋጅ ነው ብለዋል።
በቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ታፈሰ ነጋ በበኩላቸው የሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ የንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ዓላማ በአዋጁ ላይ ግንዛቤን ከመጨበጥ ባለፈ የዘርፉን ልማት በማፋጠን ከለብነት እና ብልሹ አሰራር ለመጠበቅ ሁሉም ልረባረብ እንደምገባ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም የቀረቡት ሰነዶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት አካላት መረጃን ለህበረተሰቡ በተገቢው መንገድ ማድረስ ይኖርባቸዋል በሚል የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል።
ሪፖርተር ኮከቤ ቢፍቱ
የካሜራ ባለሙያ ፈዬ ደሜ


