ህዳር 6, 2026
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ/ም (ከመልሚ)በሀገራችን የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት የተዘረጋውን የቤት ልማት አማራጭ ተጠቅሞ በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ልማት ለመሰማራት ፍላጎት ያለው የጃፓን ኩባንያ በሀገሪቱ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ ለማረጋገጥና ቅድመ-ጥናት ለማድረግ በማሰብ ወደሀገራችን ገብቷል፡፡
Fudosn Joho Bank Co.Ltd የተባለው ድርጅት ፕሬዚዳንት Mr. Tosihiro Onodera ኩባንያቸው በሪልእስቴት ዘርፍ ለመሠማራትና ከሌሎች አቅም ካላቸው ኩባንያዎች ጋር በመጣመር በጋራ መስራት እንደሚፈልግ ገልጸው አሁን በኢትዮጵያ በዘርፉ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል ለማጥናት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በሪልእስቴት ልማትና በአጠቃላይ በቤት ልማት ዘርፍ ስላሉ የተቀረጹ ፖሊሲዎችና ቢሮክራሲውን ለማሳጠር በቴክኖሎጂ ታግዘው እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች፤ የውጭ ኢንቨስትመንትን በስፋት ለመሳብ የተቀረጹ የህግ ማዕቀፎችንና የፖሊሲ ማሻሻያዎችን፤ በመንግስት የተነደፉ የቤት ልማት አማራጮችንና የተያዙ ዕቅዶችን በተመለከተ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ በአቶ ፀጋዬ ሞሼ ገለጻና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡
የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ስለተደረገላቸው አቀባበልና ስለተሰጣቸው ማብራሪያ አመስግነው በቀጣይ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ለመነጋገርና የመስክ ጉብኝት ለማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡