ሐምሌ 1, 2026

አዳማ፣ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም(ከመልሚ)

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ አመራር፣ ፋይናንስ አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የመዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽንና ማዘመን ዴስክ በ2018 በጀት አመት የመዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አፈጻጸም መሰረት በማድረግ የእውቅና ፕሮግራም አካሄዷል።

በመድረኩ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጰያ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ተሳትፈዋል።

የእውቅና መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ አመራር፣ ፋይናንስ አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደሳለኝ ገመቹ እንደተናገሩት ከተሞች የፓለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ የእድገት ማዕከላት እንደመሆናቸው መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ የህዝብ ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ይነሳሉ።

የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን እና ስታንዳርድን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የአመራሩ ቁርጠኝነት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።

እንዲሁም ስታንዳርድን ተግባራዊ ካደረጉ ከተሞች ልምድ በመውሰድ አገልግሎትን በማዘመን በቀጣይ 2019 በጀት ዓመት አገልግሎት አሰጣጥን በኦንላይን ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።

በዕለቱ የአፈጻጸም ምዘና ግብረ መልስ ሪፓርት  የምዘና ምንነት፣ የአገልግሎት አቅርቦት አፈጻጸም ምዘና ዝንባሌ፣ የአገልግሎት አፈጻጸም ጠቋሚዎች፣ የ2018 የአፈፃፀም ምዘና ማሳያዎች፣ የተስተዋሉ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች እና የምዘና ውጤት የሚሉ  ነጥቦች በዝርዝር ቀርበዋል።

በመጨረሻም የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ ከተሞች እውቅና ተሰጥቷል።

Posted in: ዜና