ነሐሴ 17, 2026
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 21ቀን፣2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለከተማ፣ መሠረተ-ልማት እና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የምስጋናና የሽኝት መርሃ- ግብር አካሄደ ፡፡
መርሃ-ግብሩ የተካሄደው የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ከሁሉም ተጠሪ ተቋማት ጋር ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት 5 ዓመታት ሴክተሩን በከፍተኛ ደረጃ በመከታተልና በመደገፍ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ከፍተቶች ደግሞ እንድሻሻሉ በትጋት ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ እንደሆነ የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል፡፡
በቋሚ ኮሚቴው ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል የኢትዮጵያ ከተሞች በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በዲጅታላይዘሽን ( አሠራርን በማዘመን)፣ በኮሪደር ልማት፣ በከተሞች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሠጠ እንደሚገኝ የጠቀሱት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፌሰር መሐመድ አብዱ ለዚህ የላቀ ውጤት መመዝገብ ትልቁን ድርሻ የተወጣው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ተናቦና ተደጋግፎ በቡድን ስሜት ስራዎችን መሥራት በመቻሉ ነው ብለዋል ፡፡
ሰብሳቢው አያይዘውም ለሴክተሩ ሁለንተናዊ ዕድገት ተቋሙን የሚመሩትና በየደረጃው የሚገኝ የመንግስት ባለስልጣን ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት በመስጠት በበጀት፣ በቴክኖሎጂና በሠው ኃይል አደረጃጀት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በመረሀግብረ ላይ እንደገለጹት ላለፉት አምስት አመታት በከተሞች የመጣው ለውጥ የዘርፉ አመራር እና መላው ሰራተኛ ዘርፉን ለመለወጥ እና የሚነሱበትን ቅረታዎች በተገቢው መንገድ ለመፍታት በቡድን መንፈስ በመስራታቸው የመጣ ለውጥ መሆኑን በማንሳት ይሄው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም በዝግጀት ምዕራፍ የተከናወኑ ስራዎችን የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡