ሚያዝያ 22, 2026

ከሚያዝያ 9-12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል  በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል፡፡

የጋራ አቋም መግለጫው በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን (CITI 2025-2050) በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የተደረገ የጋራ አቋም መግለጫ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዚዳንት ኢ/ር የሱፍ መሐመድ አቅርበዋል፡፡

መግለጫው እንዳመላከተው የኮንስትራክሽን ዘርፉ ሀገራዊ የመሰረተ-ልማትና ኢኮኖሚ ዕድገት ምሰሶ መሆኑን በመገንዘብ ዘርፉ ቀልጣፋ፣ ግልጽነት የሰፈነበት፣ ተገማች የሆነ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የባለድርሻ አካላትን ቁርጠኝነትና አወንታዊ ተነሳሽነት አረጋግጧል፡፡

ይህንን ለማረጋገጥም ስርዓታዊ አቀራረብ፣ የጋራ ባለቤትነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሁም ዘላቂነትና ፈጠራን ያካተቱ መሪ መርሆዎችን የሚከተል መሆኑን የጋራ አቋም መግለጫው አመላክቷል፡፡

ኢ/ር የሱፍ መሀመድ ባቀረቡት የጋራ አቋም መግለጫ ላይ የትብብር መስኮች እና የጋራ ቃልኪዳኖች ፣ የአስተዳደርና የሕግ ማዕቀፎች፣ የሙያ ብቃት ጥራትና ስታንዳርዶች ፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የግንባታ ግብዓቶችና ደህንነት ብሎም የትግበራ ስልቶችን አስመልክቶ በትብብርና በውጤታማነት ለመስራት የጋራ መግባባት መፈጠሩን አመላክቷል፡፡

Posted in: ዜና