ግንቦት 8, 2026

አዲስ አበባ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የክንግደም ኦፍ ኢስዋቲኒ የቤትና ከተማ ልማት ሚኒስቴር  ልዑክ በከተማ ፕላንና አሰፋፈር አመራር ስርዓት፣ በከተማ ማደስና ኮሪደር ልማት ፕሮግራሞች፣  በከተማ መሬት ልማት አስተዳደርና የካዳስተር ስርዓት እና በከተማ መሠረተልማት አስተዳደር ዙሪያ ነበር ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ነው  የልምድ ልውውጥ ያደረገው።

በቀረቡት የዘርፍ ዋና ዋና ጉዳዮች ለሀገራቸው አጠቃላይ የፖሊሲ ሪፎም ስራዎች ግብዐት የሚሆኑ ልምድ ማግኘታቸውን የክንግደም ኦፍ ኢስዋቲኒ ልዑክ ቡድን ጠቅሰው በኢትዮጵያ ያለውን ፈጣን የከተማ ልማት ስራዎች አድንቀዋል።

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ስራ አስፈጻሚው አማን አሰፋ (ዶ/ር) በሠጡት ማጠቃለያ ሚኒስቴር መ/ቤቱ መንግስት ለከተሞች ልማት በሰጠው ትኩረት ልክ አሰሪ ፖሊሲዎችን፥ ስትራቴጂዎችን እና   ዕቅዶች በመንደፍ ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች ጋር ተናቦ እየሰራ መሆኑንና ገልጸዋል።

እንደነዚህ አይነተ መድረኮች መልካም ተሞክሮ የሚቀመርበት በመሆኑ ሌሎችም የአፍሪካ ሀገራት በተመሣሣይ ተሞክሮ  እንደምቀስሙ ተናግረው  ሀገራችን  ክኢስዋቲን  የምትወስደው ተሞክሮ ስለሚኖር በእንደዚህ አይነት ኦፊሴላዊ ምክክር ብዙ መማር ይቻላል ብለዋል አማን አሰፋ(ዶ/ር)።

Posted in: ዜና