ግንቦት 8, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ጽ/ቤት ስለ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን ፤ እስካሁን  በፕሮጀክቱ የተሰሩ ስራዎች እና የመጣውን ውጠት በሚመለከት ከአንጎላ ለመጡ ልዑካን ቡድን ልምዱን አካፍሏል፡፡

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት   በ88 ከተሞች  በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ  የሚገኙ ፣ ስራ የሌላቸው፣ አካል ጉዳተኛ እና አረጋዊያን  የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚደግፍ ሰው ተኮር  ውጤታማ ፕሮጀክት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በአለም ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በፌዴራል እና በክልል ከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ሁነታ ውስጥ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ በማድረግ በአረንጓዴ ልማት፣ በከተማ ውስጥ ጽዳት ፣ በከተማ ግብርና እና መሰል የአከባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ በማሰማራት በልዩ ትኩረት የሚሰራ ፕሮጀክት እንደሆነ እና  መንግስት የዘጎችን ኑሮ ለማሻሻል ከምሰራቸው ስራዎች እጀግ ውጤታማ ፕሮጀክት እንደሆነ ለልዑካኑ ተገልጿል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በቆይታቸው በአካባቢ ልማትና በኑሮ ማሻሻያ የተሰሩ ስራዎችን በከተሞች ምልከታ የሚያደርጉ ሲሆን በመጨረሻም  ከአለም ባንክ እና ከሌሎች  የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የከተሞች ምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተሾመ ተናግረዋል፡፡

Posted in: ዜና