ግንቦት 20, 2026

አለም ገና፣ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተመርጠው ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሪፎርሙን ወደ ትግበራ ለማስገባት ባለፉት 10 ወራት በርካታ ተግባራት ስያከናወኑ ቆይተዋል።

ሪፎርሙ ውጤታማ፣ ምላሽ ሰጪ እና ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር የመላመድ፣ የትብብር፣ የስነምግባር ባህሪ እና ህዝብን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለመፍጠር የገቢር-ነበብ አመራር (Pragmatic Leadership) ለመፍጠር፣ የምሰራ እንደሆነ በመድረኩ ላይ የተገኙት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።

በሂደትም የተቋም ግንባታ ማለትም በሰው ኃይል፣ ተቋማዊ መሪነትና የተቋሙ የካበተ የአሠራር ሥርዓት፣ የተቋም የሥራ ባህልና እሴቶች፣ ዕቅዶችን ለማስተግበር ተግባራቱ የሚከናወኑበት ሂደትና ሥርዓት፣የተቋማዊ መሠረተ-ልማት፣ ሀብቶች፣ በተቋሙ ሥራን ለማቀላጠፍና ለማገዝ ዝግጁ የሆኑ ፋሲሊቲዎች ማሻሻልን ያካትታልም ብለዋል ክብርት ሚኒስትር ።

የርፎርሙ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ወ/ሚካኤል ባቀረቡት ሪፓርት ባለፉት 10 ወራት ሪፍርሙ የሴክተሩ ቁልፍ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ሁለም በኃላፊነት እና ጊዜ የለንም በሚል አግባብ እንቀስቀሰ በማድረግ በጥብቅ ዲሲፒሊን መምራት መቻሉንና የሪፍርሙ ተሞክሮ በአንደኛው ዙር ተግባራዊ ካደረጉ ተቋማት በተደራጀ ሁኔታ የመቀመር፤ ለሪፍርሙ ስኬት ሀብት የማሰባሰብ ተግባር መፈፀም፣ የሪፍርሙን ተግባራት የተሳካ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ ሪፎርሙን ሕዝባዊና ተቋማዊ ለማድረግ ከዘርፉ ሠራተኞች፣ ከአመራሮች፣ ከባለድርሻ አካላት፣ ከክልሎች፤ ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከልማት አጋሮች ጋር ተደጋጋሚ መድረኮችን በመፍጠርና ውይይት በማድረግ የሪፎርሙን የረጅም ጊዜ ውጤትና ለሀገር ብልፅጽግና ዕድገት ያለውን ጠቀሜታ ለማስገንዘብ ተሞክሯል ብለዋል አቶ ተስፋዬ፡፡

ስለ ሪፍርሙ ዓላማ እና ጥቅሞች ትክክለኛና ግልፅ መረጃ ለመስጠት መቻሉን እና
አመራሩና ሠራተኛው ሪፍርሙን በባለቤትነት እንዲመሩት ሌሎች አካላት ደግሞ ጠንካራ ድጋፍ እንዲሰጡ የማድረግ ሥራዎች መሥራታቸውንም እንዲሁ ።

የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፍርሙን ተግባራዊ ለማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች፣ በመረጃ አያያዝ፣ በሳይበር ደኅንነት እና በተዘማጅ ሥራዎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በፍጥነት ማሰካት መቻሉንም በሪፓርቱ ተገልጿል ፡፡

ተጠያቂነት፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚችል ነጻ፣ ገለልተኛ፣ አካታች ሲቪል ሰርቪስ መገንባት ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት እስካሁን ያሳዩት እርብርብ ብርቱ እና ውጤታማ ነበር ያሉት የፈደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን ም/ኮምሽነር ወ/ሮ አልማዝ መሰለ ነገር ግን በትግበራ ምዕራፍም ይሄው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ሪፎርም ማካሄድ የምርጫ ጉዳይ እንዳልሆነ ተገንዝበን ወደ ተግባር መግባት አስፈላጊ በመሆኑ፣ የሪፍርሙ የዝግጅት ምዕራፍ ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ጫፍ መድረሳችን በመገምገም ወደ ትግበራ ምዕራፍ በመግባት የሪፎርሙን ግብ ለማሳካት የሪፎርም አመራሩ ለውጥ ያስፈለገበትን ምክንያት ማወቅ ወይም መገንዘብ ፣ ለውጡን ለመደገፍ እና በለውጡ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየት ፣ ለውጡ እንዴት እውን እንደሚሆን ማወቅ ወይም መረዳት ፣ ለውጡን የመተግበር ችሎታ ወይም ብቃት፣ ለውጡን በዘላቂነት ማስቀጠልና የተቋማትን የሩቅ መዳረሻ መተለም ዋና ዋናዎቹ የትኩረት አቅጣጫዎቻችን በማድረግ እንድሰራ ክብርት ሚኒስትር በማጠቃለያው አሳስበዋል፡፡

Posted in: ዜና