ሐምሌ 27, 2026
መተሐራ(ቤይኑና)፣ ሐምሌ 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሠረተ-ልማት ዘርፍ የተጠሪ ተቋማት 2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸማቸውን እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዳቸውን በጋራ ገምግመዋል፡፡
ተቋማቱ በተለይ ያለፈውን በጀት አመት አበይት ክንውኖች ያሏቸውን እና የቀጣይ በጀት አመት 2019 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር የመሠረተ-ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) እንደተናገሩት ባለፈው በጀት ዓመት የተገኙ ምረጥ ተሞክሮዎችንና አፈጻጸሞችን በቀጣይ ዓመት የበለጠ አጠናክሮ በማስቀጠል ክፍተቶችንና ተግዳሮቶች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አመራሩና ባለሙያው የየበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሙአዝ በድሩ (ዶ/ር) የባለስልጣኑን 2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ዝግጅት፣ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን የክትትልና ድጋፍ ስራ፣ የሥራ ላይ ድህንነት በተገቢው መንገድ መተግበሩ፣ የቁጥጥርና የግምገማ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኢኒሼቲቭ ፣ የአቅም ግንባታ፣ የድጅታላይዘሽን አሠራርን ተግባራዊ በማድረግ በተለይ የሞሰብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን እና የኮንስትራክሽን ግጭት አፈታት ሥራ መሠራቱን ም/ ዋና ዳይሬከተሩ ገልጸዋል ፡፡
የኮንሰትራክሽን ማነጅሜንት ኢንስትቲዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ኢንጂ.ቅድስት ማሞ የበጀት ዓመቱን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የድጅታላይዘሽን አሠራርን ተግባራዊ በማድረግ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ከገጠር መንገድ ትስስር ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት መሠራቱ፣ የልህቀት ማዕከል ግንባታ አፈጻጸም፣ ከተለያዩ የውጭ ተቋማትና የሀገር ውሰጥ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት መደረጉ፣ ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት እንዲተካ በማድረግ የቴክኖሎጅ ሽግግርና ጥናት ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ማጥናት ፣ የተለያዩ ፌደራል ፕሮጀክቶችን የማማከር አገልግሎት፣ ከ14 በላይ ስታንዳረዶችን ማስተዋወቅ መቻሉ፣ የ3ዲ ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬከተር ኢንጂ. ሂሩት ዮሐንስ የበጀት የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት የተጀመሩ ሀገራዊ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደስራ መገባታቸው፣ ዉጤታማ የሀብት አጠቃቀም መኖሩ፣ በመንገድ ሥራ የመልካም አስተዳደር ስራዎች የዜጎችን ቅሬታ በተገቢው መንገድ መፍታ መቻሉ፣ ሠራተኛውንና አመራሩን በሥነ-ምግባር ለማነጽ አሠራ መዘርጋቱ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጅን እውን ማድረግ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣ የምርምርና ጥናት ስራዎችን ወደ ፕሮጀክት ማሳደግ መቻሉ፣ የመንገድ ሽፋን ማሳደግ መቻሉ፣ የፕሮጀክት ግንበታዎች መፋጠን መቻላቸው፣ ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የገጠሙትን ተግዳሮቶች በገለጹበት ወቅት በተለይ በነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ በተለያዩ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር፣ የበጀት እጥረት፣ የመንገድ ብልሽት፣ የወሰን ማስከበር ችግር፣ የክፍያ መጓተት፣ የፕሮጀክት አስተዳደር ችግር፣ የምህንድስና ግዥ ችግር፣ ከክብደት በላይ የሚጭኑ ተሸከርካሪዎች መበራከት፣ የመሬት መንሸራተት እና የማሽነሪ እጥረት፣ በዋናነት ተቋሙን እየፈተኑት እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን በማናበብ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከሁሉም ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተፈራርመዋ፡፡