ህዳር 6, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም (ከመልሚ)በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በቤቶችና ከተማ ልማት ዘርፍ ስር የሚገኙ መሪ ስራ አስፈጻሚዎች ስራ ክፍላቸውን  የ2019 በጀት ዓመት እቅድና የ1ኛው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከዘርፉ ሚኒስትር ደኤታ ጋር ውይይት ተካሄዷል።

ሪፓርት የቀረበባቸው የቤቶች ልማት ፣የከተማ መሰረተ ልማት እና የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት፣ ግመታና ፍቃድ መሪ ስራ አስፈጻሚ  ናቸው። ለቀጣይ የስራ ጊዜ ዘርፉን በመረዳት እና ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ተካሄዷል።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶችና ከተማ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከዘርፋ  የስራ ክፍሎች የቀረቡ እቅድና ሪፓርት መሰረት አርገው ሀሳብ ሰጥተዋል።

ሁለተኛው እና ሶስተኛው ሩብ አመት ቁልፍ የትግበራ ምዕራፎች ሲሆኑ በመደመር መንግስት የእያንዳንዱ ዜጋ ችግር መፍታት የሚያስችሉ ጉዳዮች በእቅድ ውስጥ በማካተት ቅኝት የሚደረግበት እና የእቅድና ሪፖርት ስራዎች ተመጋጋቢ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከክልሎች፣ ከከተማ አስተዳደርና፣ እና  ከዘርፎች  ጋር በተያያዘ የማናበብ ስራዎች መስራትና የተለየ ትኩረት የሚፈልጉ ስራዎችን በመለየት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሚመጥኑ ስራዎች መስራት ይገባል ብለዋል ክቡር ሚኒስትር ደኤታው ፡

Posted in: Uncategorized ዜና