ሰኔ 15, 2026
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ዘርፍ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆንና ዘርፉ ሰፊ እና ውስብስብ እንዲሁም ብዙ ሀብት የሚንቀሳቀስበት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የሚኒሱ ጥያቄዎችን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል፡፡
የውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት ክቡር ሚ/ዲኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በዘርፉ የወጡ አዋጆች ደንቦች እና መመሪያዎች በማጣራት ተመጋጋቢ እና ተናባቢ በማድረግ ወጥነቱን አስጠብቆ መሬት በማውረድ ከጥያቄ ባለፈ ተግባራዊ ማድረግ እንደምገባ ተናግረዋል ፡፡
በውይይቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ሙሉዓለም ደበበ ለህንጻ ስራ ተቋራጮች፣ ለሙያ ማህበራትና ለአማካሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የስራ ክፍሉ በሰጠው ስልጠና የተነሱ ጥያቄዎች፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የኮንስትራክሽን የምዝገባና የብቃት ማረጋገጫ መመሪያ ረቂቅ እንዲሁም ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የመወያያ ሰነዶች አቅርበዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት በማፋጠን የመሰረተ ልማት አውታሮችን በመዘርጋትና ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ያለው ከፍተኛ ድርሻ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዘርፉ የሚከናወኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች የሚጠበቅባቸውን ጥራት፣ ደህንነት እና የወጪ ቆጣቢነት መርህ ተከትለው እንዲከናወኑ ለማድረግ ዘመናዊ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
የኮንሰትራክሽን ኢንዱስትሪ መረጃዎችን እና ግብዓቶችን በአንድ ቋት ማግኘት የሚያስችል እና የዘርፉ ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ችግር የሚፈታ ሲስተም በሚዲያ ላይም ዘርፉ ከማስተዋወቅ ጋር በተያያዘ በርካታ ስራዎችን እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡
በውይይቱ ላይ የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች እና የዘርፉ አመራሮች ተሳትፈዋል።