ሐምሌ 1, 2026
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም(ከመልሚ
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሂደት፣ ስኬት እና ድህረ-ምርጫ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒሰትር ዲኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንደተናገሩት በስኬት የተጠናቀቀው ሀገራዊ ምርጫው ነጻ ፍትሐዊ እና ሠላማዊ መሆኑ መንግስትና ፈጻሚው አካል የነበራቸውን አበርክቶ ላይ ለመምከር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
በምርጫ ሂደት መንግስት ከተመሠረተ በኋላ ደግሞ የጋራ ሀገርን ለመገንባት ብርቱ ትብብር ከመላው ሕዝብ እንደሚጠበቅ ክቡር አቶ ፈንታ ገልጸዋል።
የሃሳብና የፖለቲካ ልዩነቶች ቢኖሩም ሀገርንና ብሄራዊ ጥቅምን በማስከበር ረገድ በጋራና በትብብር ለአንድ ሀገራዊ አላማ መቆም እንደሚያስፈልግም ደግሞ የገለፁት የውይይት ሰነድ ያቀረቡት ክቡር ሚኒስትር ደኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ናቸው።
ምርጫ በባህሪው የውድድር እና የፉክክር ጉዳይ ቢሆንም ለአንድ ሀገር ግንባታ እስከሆነ ድረስ ወደ ትብብር መቀየር ይገባል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት ምርጫው የተሳካ እንዲሆር በርካታ ስራዎች እንደተሰሩም ክቡር ሚኒስትር ደኤታ ገልጸዋል፡፡
የድህረ ምርጫ ተግባራትን በውጤታማነት በማከናወን ጠንካራ ስርዓተ መንግስት የመገንባት ሀገራዊ ግብን ማሳካት ዓላማ ያደረገ ውይይት እንደሆነና የጋራ ግንዛቤ መፍጠር፣ ህገ ወጥ ድርጊቶችን መከላከል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ፡፡
በመጨረሻም የመወያያ ሰነዱን አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን ምላሽ እና የቀጣይ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡