ነሐሴ 17, 2026
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ ተግባራዊ ተሳትፎ እያደረገ ነው፡፡
የሚኒስቴሩ ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች የችግኝ ተከላውን ያካሄዱት በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሦሥት ነው፡፡
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የራሷን ኀላፊነት በተግባር እየተወጣች ነው ብለዋል።
የተተከሉት ችግኞች አድገው ጥቅም ላይ እስከሚውሉ ከሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት እና ከሴፍትኔት አባላት ጋር ክትትል እና እንክብካቤ እንደሚደረግም ገልጸዋል።