ጥቅምት 13, 2026
አዲስ አበባ ጥቅምት 2፣ 2019 ዓ.ም(ከመልሚ) በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) የኢፌዲሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ክቡር ኢንጂ.ሙሀመድ አብድራህማን ከክብርት ጫልቱ ሳኒ ጋር የሥራ ርክክብ አደረጉ፡፡
ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በርክክቡ ወቅት እስካሁን ስለ ተከናወኑ ሥራዎች አፈጻጸም፣ ተጀምረው በሂደት ላይ ስለሚገኙ ሥራዎችና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው፣ በተገኘው ውጤትም እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢንጂ.ሙሀሙድ አብድሪህማን እንደ ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎችና መሠረተ ልማቶች፣ የከተማውን ሕብረተሰብ ጥያቄ በአግባቡ የሚመልሱ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ሳይስተጓጎሉ በአመራር ቅብብሎሽ በተሻለ መንገድና ፍጥነት እንደሚቀጥሉ ተናግረው የተረከቧቸውን ሀገራዊ ኃላፊነቶች በብቃት ለመወጣትና ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በትውውቅ እና ርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል ፡፡