ጥር 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከአዛርባጃን ሪፐብሊካ አምባሳደር ጋር እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ግንቦት 24 ቀን 2026 
በአዛርባጃን ባኩ ከተማ በሚካሄደው 13ኛው የዓለም ከተሞች ፎረም ተሳትፎ ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል፡፡

በፎረም ላይ የኢትዮጵያን ከተሞች ተሞክሮ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ማቅረብ በሚችልበት ሁኔታም ተወያይተዋል ፡፡

የዓለም የከተሞች ፎረም በየሁለት ዓመቱ እንደሚከበርና የዘንድሮውን ዓመት የምታዘጋጀው ሀገር አዘርባጃን ከተማዋ ደግሞ ባኩ ስትሆን የፎረሙ አስተባባሪው ዩ ኤን ሀቢታት ነው።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የከተሞች ፎረምን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በማዘጋጀትና እንደሀገርም የከተሞች ፎረምን ለ10ኛ ጊዜ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት በሰመራ
ሎጊያ ከተማ በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ማዘጋጀት መቻሏ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተሞክሮዋን ይዛ ብትቀርብ ሀገሪቱ የጀመረቻቸውን ፈጣን የልማት ስራዎች ማሳያ እንደሚሆን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ኢትዮጵያ ለምታዘጋጃጀቸው ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችና የከተማ መሠረተ-ልማቶችን አስመለክቶ በርካታ ልምድና ተሞክሮዎች የሚገኙበት ታላቅ መድረክ በመሆኑ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ እድሉን እንደምጠቀምበት አምባሰደር ሩስላን ናሲቦቭ ተናግረዋል ፡፡

Posted in: ዜና