የካቲት 20, 2026

አዳማ፣ የካቲት12፣ 2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) ኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ የትስስር ፎረም የዕቀድ አፈጻጸም ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄዷል፡፡

ፎረሙን ከመንግሰታዊ ተቋማት በዋናነት የሚመሩት ትምህርት ሚኒስቴር፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ናቸው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የምርምር ተቋማት፣ የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት፣ የግል አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የዘርፍ ማኅበራት፣ የሙያና ሲቪክ ማኅራት በተሳተፉበት መድረክ ፎረሙ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው የተመሠረተው ፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር) እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና በምርምር ተቋማት መካከል ትብብረን፣ ቅንጅታዊ አሠራር ዘላቂ በሆነ መንገድ በጋራ መሥራቱ ለሀገራዊ እድገትና የትውልዱን መጻኢ ዕድል ለመወሰን ሚናው እጅግ የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።

ተጠቃሚነትን፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሙህራንና አሠልጣኞች የኢንዱስትሪ ተሞክሮ ጉድኝትን አጠናክሮ ለመቀጠል ፎረሙ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል ሚ/ደኤታው ፡፡

የኮንሰትራክሽን ኢንዱስትሪው በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ለዘረፉ የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት የዘርፉ ተዋኒያን በትስስር መሥራት ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው ያሉት የፎረሙ ተሳታፊዎቹ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያገኙትን እውቀት ወደተግባራዊ ልምምድ ሲሄዱ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሠማሩ ኩባኒያዎች ለተማሪዎቹ ተገቢውን ክህሎት ጨብጠው እንዲወጡ የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ከውጭ ሀገራት የምናስገባቸውን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በእውቀት አስታጥቀው ከመላክ ጎንለጎን በተለያዩ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በተግባራዊ ልምምድ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ መተባበር መደጋገፍ፣ መቀናጅተን እንደመርህ ይዞ መሥራት ይገባልም ብለዋል፡፡

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ኢንዱስትሪው በጥራት፣ በምረታማነተነትና በተወዳዳሪነት ጎልብቶ እንዲወጣ  የከፍተኛ ትምህርት የበቃ የሰው ሃይል በክህሎትና በአመለካከት  የበቃ ትውልድ መቅረጽ እንዲችሉ የፎረሙ አባላት ቅንጅታዊ አሠራረቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡

በመጨረሻም የተዘጋጀው መተዳደሪያ ደንብሰ ውይይት ከተደረገበት በኋላ መስተካከል ያለባቸው ነጥቦች ተስተካክለው በሙሉ ድምጽ በማጸደቅ የእለቱ መርሀ ግብር ተጠናቋል ።

Posted in: ዜና