ሐምሌ 27, 2026

ከሚሴ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው “የከተሞች ልማትና ኮንስትራክሽን ስለኢትዮጵያ” በከሚሴ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በአገራችን እየተፈጠረ ያለውን ፈጣን የከተሜነት ዕድገት በአግባቡ ለመምራት የከተማ ልማት ሥራችንን አሁን ከደረስንበት የዕድገት ደረጃ፣ የዜጎች ፍላጎት እንዲሁም አገራዊ ርዕይ መነሻነት ሁሉንም ሴክተሮች በማቀናጀት የዕድገት አማራጮችን ማስፋትና ማጠናከር ወሳኝ የሆነ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

የከተማ ልማት ሥራ ባለ ብዙ ዘርፍ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ በመሆኑ የኢንዱስትሪ፣ የገበያ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማትና አገልግሎቶችን በቅንጅት፣ በትስስርና በተመጋጋቢነት በውስጥም ሆነ ከአካባቢው በጋራና ትብብር በመፍጠር መምራትን የሚጠይቅ እንደሆነም ገልጸዋል ፡፡ 

“ስለ ኢትዮጵያ” የፓናል ውይይት እና የፎቶግራፍ ዐውደ-ርዕይ የሚቀርብበት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚካሄድ ሀገራዊ የውይይት መድረክ ሲሆን ዓላማውም የውይይት እና የመነጋገር ባህል እንዲዳብር እና ብሄራዊ ትርክት ለመገንባት ያለመ ቀጣይነት ያለው ፕሮግራም በመሆኑ ልዩ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ተናግረዋል።

Posted in: ዜና