ሚያዝያ 22, 2026

አዲስ አበባ ሚያዝያ 12/2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የኢትዮጵያ መሠረተ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሳምንት (EICW) በተለያዩ የፓናል ውይይቶች እና ታላቅ ኤግዚቢሽን ታጅቦ ውጤታማ የትብብር መድረክ መሆኑን አስመስክሯል።

በኢነርጂ፣ በትራንስፖርት፣ በዲጂታል ሥርዓት፣ በማዕድን እና በኮንስትራክሽን ዘርፎች በተዘጋጁ የፓናል ውይይቶች እና የኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን ላይ ባለድርሻ አካላት የሀገራችንን የመሠረተ ልማት እድገት የቃኙበት እንዲሁም ካለፈው በመማር የወደፊቱ እቅዶቻችንና ትልሞቻችንን የዘረጋንበት ነው ስሉ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በሁነቱ ላይ በልዩ ሁኔታ የታየው በመረጃ ላይ የተደገፈ ጥልቅ ትንተና እንዲሁም በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ እና በልማት አጋሮች መካከል የታየው ተግባራዊ ትብብር ሲሆን፤ ይህም በውይይቶች የተለዩ ተግዳሮቶችን እና ዕድሎችን ወደ ጋራ ጥረት እንዲቀየሩ ማስቻሉንም ተናግረዋል ሚኒስትር ደኤታው ።

የኤግዚቢሽን መድረኩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እና የፈጠራ ሥራዎችን በግልጽ ያሳየ ሲሆን፣ የተደረጉት ውይይቶችም ከዕቅድ ወደ ተግባር እንዴት መሸጋገር እንደሚቻልና ጥልቅ ቅንጅት ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን ፈጥሯልም ብለዋል።

በአጠቃላይ EICW 2026 የዘርፉን የለውጥ ሂደት ያንጸባረቀ ሲሆን፤ ይበልጥ የተሳሰረ፣ ለፈጠራ ክፍት የሆነ እና የተያዙ ታላላቅ ግቦችን በተቀናጀ ሀገራዊ አፈጻጸም ወደ ውጤት ለመቀየር ትኩረት የተሰጠበት መድረክ ነበር።

ፈጠራ፣ ፍጥነት እና ጥራት ለመሰረተ ልማት እመርታ
ኢትዮጵያ ትገነባለች!

Posted in: ዜና