ሐምሌ 27, 2026

በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ተጠሪነታቸው ለከተማ አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑ የስራ ክፍሎች በዛሬው ዕለት በቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የጋራ ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት አካሄዱ፡፡

በፊርማ ስነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የስራ ክፍሎች ለዘርፉ ተጠሪ የሆኑት የመሬትና ካዳስተር መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የከተማ ፕላንና አከታተም መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የከተማ አመራር፣ ፋይናንስና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ፤  የከተሞች ምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ጽ/ቤት እና የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ናቸው፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ስናቅድ በተቋም ደረጃ እየተሰራ ያለውን ሪፎርም ማዕከል ባደረገ የበቃ የሰው ኃይልን ተጠቅሞ ስራን ለማቀላጠፍና የተገልጋዩን ዕርካታ ለማሳደግ የተያዘውን ሀገራዊ ራዕይን የምናሳካበትና በ2030 ስራዎችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ በማድረግ ወረቀት አልባ አሠራርን ዕውን የምናደርግበት ስለሆነ አመራሩና ሠራተኛው በዚሁ ልክ ግንዛቤው ኖሮት ስራውን ማከናወን እንደሚጠበቅበት ገልጸው ሁሉም አመራርና ሠራተኛ የሪፎርሙን ዓላማ ተገንዝቦ የመፈጸም አቅሙን ለማሻሻል ከወዲሁ ጥረት ማድረግ እንደሚገባው ገልጸው ዘርፉን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ተቋማዊ ለማድረግ እንዲቻል የሰው ኃይል አቅምን ማጠናከር፤ አሠራርን በቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግ፤ ስራን በትብብር መንፈስ፣ ተቀናጅቶ በመስራት የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Posted in: ዜና