ሐምሌ 8, 2026
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ሀገር በቀል የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎችን አምራች አካላትን ለመደገፍ ለማበረታታት ጥረት እያደረገ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም ጌታቸው እና ናትናኤል የፈጠራ ህብረት ሽርክና ማህበር በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ስታንዳርድ የወጣለትን የተንቀሳቃሽ ዘመናዊ ፓተንት ራይት ያለው ለአካል ጉዳተኞችም ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ ደብሊው ሲ(Toilet Seat With Afloating Mechanism)መጸዳጃ ቤት በማምረት፣ በማስጠቀም እና በማከፋፈል የሚሰራ ማህበር በመሆኑ ይህንን ቴክኖሎጂ በመስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ባለሙያዎች የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡
በጉብኝቱ ለማየት እንደተሞከረው መጸዳጃ ቤቶቹ በሀገር በቀል የፈጠራ ውጤቶች የተሰሩ ሲሆን ለአቅመ ደካሞች፣ ለነብሰጡር ሴቶች እና ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ህዝብ በበዛባቸው አካባቢዎች አገልግሎት የሚሰጡና ተንቀሳቃሽም እንደሆኑ ለማየት ተችሏል።
መጸዳጃ ቤቶቹ፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች በብዛት በሚገኙበት የእርዳታ ማዕከላት በስፋት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የኮሊደር ልማት ተግባራዊ በተደረገባቸው ከተሞች ተደራሽ በማድረግ የማህበረሰቡን ህይወት በእጅጉ የሚያቀሉ ናቸው።
በጉብኝቱም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ካሊድ አብዱራህማን እንዳሉት የተሰራው የፈጠራ ስራ የሚበረታታ ሲሆን በስፋት መስራትና ተፈላጊ መሚሆኑበት አካባቢ አቅርቦቱን ማስፋፋት ያስፈልጋል።
እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የፈጠራ ስራው በተለያዩ መድረኮች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ከመስራት ባለፈ በምንችለው ሁሉ እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሙሉዓለም ደበበ በበኩላቸው የፈጠራ ስራው ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር እና ለአጠቃቀም ቀላል በመሆናቸው የተጠቃሚውን ጫና የሚያቀሉ ናቸው።
ከጥራት እና ከውበት ጋር በተያያዘ እስታንዳርዳቸው የጠበቁ መሆኑን ይኖርባቸዋል በማለት ለአካል ጉዳተኞች እና ለነብሰጡር ሴቶች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከመሆኑም ባለፈ ተንቀሳቃሽ መሆናቸው የሚበረታታ የፈጠራ ውጤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።