መስከረም 4, 2026

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚ/ድኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን የናሚቢያን የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣  ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የናሚቢያ የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ሳንኳዋሳ ጀምስ የተመራ  ልዑካን ቡድኑ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በከተሜነትና  ክትመት፣ በከተማ ፕላን እና በቤት ልማት ዙሪያ  የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ 

ልምድ ልውጡን አስመልክተው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንዳሉት የኢትዮጵያና የናሚቢያ ግንኑነት  ታሪካዊ መሆኑን ገልጸው በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ  የትብብር ስራዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት  እየሰራች መሆኑን ተናገረዋል።

በተለይ በአየር ትራንስፓርት አገለግሎት የተደረሰው ስምምነት ትለቁና ዋነኛው መሆኑን ገልጸዋል ክቡር ሚኒስትር ድኤታው፡፡

በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በቱሪዝምና በኢንቨሰትመንት እየታያ ያለውን መነቃቃት በማስፋት የሁለትዮሽ የንግድ ለውውጥን ከግምት በማስገባት ለጋራ ብልጽግና መስራት እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ፈንታ አስገንዝበዋል፡፡

የከተማ የተቀናጀ ፕላንና ተመጣጣኝ የሆነ የቤት ልማት ላይ እየታየ ያለውን ተሰፋ ሰጪ ዕድገት ለናሚቢያ የልዑካን ቡድን አባላት  ስናጋራ እጅግ በጣም በደስታ ነው ብለዋል፡፡

የናሚቢያ የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ሳንኳዋሳ ጀምስ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በከተማ ፕላንና በቤቶች ልማት ብሎም በከተማ ውበትና ጽዳት ባዩ ት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው፣ ለዑካን ቡድናቸው የቀሰሙትን ተሞክሮ በሀገራቸው ላይ ወስደው እንደሚተገብሩት ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

ከተሜነትና  ክትመት በኢትዮጵያ፣ የከተማ ፕላን እና የቤቶች ልማት ያለበት ነባራዊ ሁኔታ  በተሞክሮነት ለናሚቢያ የልዑካን ቡድን አባላት ቀርቧል።

Posted in: ዜና