ሐምሌ 1, 2026
አርባ ምንጭ፣ ሰኔ 20 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም ክልል የዘርፍ የስራ ኃላፊዎች እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ጫልቱ ሳኒ የሀገሪቱን ከተሞች ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ለማሻገር ከመቸውም ጊዜ በላይ መልካም ዕድልና አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል።
የከተሞች የመልማት ዕድል ተጠቅሞ የየትኛውም የከተማ አመራር ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል ክብርት ሚኒስትር።
የከተማ ልማት ሥራ ባለ ብዙ ዘርፍ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ በመሆኑ የኢንዱስትሪ፣ የገበያ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማትና አገልግሎቶችን በቅንጅት፣ በትስስርና በተመጋጋቢነት በውስጥም ሆነ ከአካባቢው በጋራና ትብብር በመፍጠር መምራትን የሚጠይቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ነው ብለዋል ክብርት ሚኒስትሯ፡፡
ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው በርካታ ስራዎች መካከል የከተሞችን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ፣ ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሃዊነት የሰፈነበት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት በማጎልበት፣ ከከተሞች ገፅታ መቀየር፣ ነዋሪውን የቤት ባለቤት እንዲሆን ከማድረግ ጋር የተያያዘ የቤት ልማት ፕሮግራም በመተግበር፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ተወዳዳሪ ከተሞች መፍጠር ነው ብለዋል ክብርት ሚኒስትር።
በፕላን የሚመሩና ደረጃቸውን የጠበቁ ከተሞችና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እንዲኖሩና አገልግሎቶችን በአግባቡ እንዲቀርቡና እንዲዘምኑ እንዲሁም የነዋሪው እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር በማድረግ፣ የከተሞችን መሰረተ ልማት በማስፋፋት እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት እንዲያፋጥኑ በማድረግ ረገድ ከባለፉት ዓመታት በተሸለ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ክብርት ሚኒስትሯ ገልጸዋል ፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ የሀገሪቱን ከተሞች ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ለማሻገር ከመቸውም ጊዜ በላይ መልካም ዕድልና አጋጣሚ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ይህንን መልካም የከተሞች የመልማት ዕድል ተጠቅሞ የየትኛውም የከተማ አመራር ትኩረት ሰጥቶ ሊተገብረው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የእንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ከቡር መስፍን መንዛ( ዶ/ር) የአርባ ምንጭ ከተማ በተፈጥሮ መስህብ፣ ለቱርሲት ጎብኝዎች እጅግ የታደለች ከተማ ከመሆኗ በላይ የሰላምና የፍቅር ከተማ መሆኗን ጠቅሰው ዘመኑ የከተሞች የመልማት ዘመን በመሆኑ በሀገር ውስጥም ሆነ በሀገር ውጭ ያሉ ዜጎች ሀብታቸውን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸምና የቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ አቅጣጫን የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን በዝረዝር አቅርበዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሁሉም ክልሎች ባደረገው ክትትልና ድጋፍ ከተሞች ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገቡ እደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡
ለዚህም ማሳያው በኮሪደር ልማት፣ በሌማት ቱርፋት፣ በገበታ ለሀገር እዲሁም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እየተመዘገበ የመጣው ዕድገት በአጠቃላይ የከተማው አመራር ካለፉት ዓመታት በበለጠ ለከተማ ስራ ትኩረት ሰጥቶ መስራት በመቻላቸው ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ የከተማ ልማት ፖሊሲ በአማን አሰፋ (ዶ/ር) የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ(ዶ/ር) ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት እቅድን የጋራ በማድረግ የመግባቢያ ሰነድ ክልሎች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በመፈራረም መርሀ ግብሩ ተጠናቋል።