ጥቅምት 13, 2026
ቢሾፍቱ፣ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም (ከመልሚ) አህጉር አቀፍ የሆነው የአፍሪካ ከንቲባዎች ፎርም በቢሾፍቱ ከተማ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ለቀጣይ ተከታታይ ቀናት በቢሾፍቱና በአዲስ አበባ ከተሞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
ይህ አህጉር አቀፍ ፎረም ከ55 በላይ የአፍሪካ ከተማ ከንቲባዎች እና በሀገር ውስጥ የ15 ከተሞች ከንቲባዎች የተሳተፉበት እና በከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚመጣውን ለውጥ መሰረት በማድረግ የልምድ ልውውጥ ለማድረግም የሚያስችል ፕሮግራም እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ በቢሾፍቱ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች፣ የኮሪደር ልማት በከተማው ያመጣው ለውጥ፣ የተፈጠረው የስራ እድል እንደ አጠቃላይ በከተማው የሚታየው ለውጥ የከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ያስጎበኙ ሲሆን በከተማው የቆይታ ጊዜያቸው የመድረክ ፕሮግራሞችና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ተዘዋውረው ምልከታ እንደሚያደርጉ ከንቲባው አያይዘው ተናግረዋል፡፡
የአፍርካ ከንቲባዎች ፎረም አስተባባሪ ያሬድ ተሾመ(ዶ/ር) እንዳሉት የከንቲባዎች ፎረም ሶስት ዓላማዎችን መሰረት ያደረገ ሲሆን እነዚህም ከንቲባዎችን የማብቃት፣ ከተሞች ድጅታላይዝ የሆነ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግና የኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሆኑ ማስቻል ነው ብለዋል፡፡
ሮረሙ በተለያዩ ፕሮግራሞች ለቀጣይ ለተከታታይ ቀናት በቢሾፍቱና በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡