ነሐሴ 17, 2026
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት በዌቭ ሁለት የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርምን ላለፈው አንድ ዓመት ስያከናውኑ የነበረውን የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ሪፖርት በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተባባሪነት ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ አካላት አቅርቧል፡፡
የሪፎርሙን የዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቅ አስመልክቶ የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንደተናገሩት በተቋሙ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች በዚህ ሪፎርም ከፍተኛ አቅም መፈጠሩንና የሴክተሩን መሠረታዊ ችግሮች ሊፈታ በሚችል መልኩ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በከተሞች ፈጣን ዕድገት ለማምጣት በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ የከተማ ነዋሪዎች ክብራቸውን የሚመጥን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ተጠያቂነት ያለበት አገልግሎት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ የድጅታላዘሽን አሠራርን እውን በማድረግ የሀገሪቱን ከተሞች የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ሪፎርሙ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ውይይቱን ያካሄዱት የሚኒስቴር መስሪ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የቴክኒክ ኮሚቴዎች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በጋራ በመሆን ከሲቪል ሰርቪስ ኮሙሽን፣ ከጠቅላይ ሚበኒስቴር ጽ/ቤት፣ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ የኮሚቴ አባላት ለአንድ ዓመታት ያህል ስደረግ የነበረውን የሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ኮሚቴው ተቋሙ ላለፉት አስራ ሁለት ወራት ያከናወናቸውን የርፎርሙን የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እና ጥናቶች በአካል ምልከታ አድርገዋል