ሚያዝያ 22, 2026
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሊደር ልማት እስከ 76 ከተሞች ተደራሽ የተደረገው የከተሞችን ገጽታ በእጅጉ የቀየረ ሲሆን የቤት ልማትንም የሚያካትት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ የቤት ልማት ፖሊሲ እና የኮሪደር ልማትን አስመልክተው በመሩት የፓናል መድረክ የቤት ጉዳይ የከተማውን ነዋሪ አንገብጋቢ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በተለይ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ 1.5 ሚሊየን ቤቶች በአምስት አመታት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከዚህ ባሸገር ከተሜነት የምንመርጠው ወይም የሚቆም አይደለም።ሀገራችን በከፍተኛ የክትመት ምጣኔ ላይ ትገኛለች ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ክቡር ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኮሪደር ልማት በአዲስ አበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ የተደረገው አዲስ አበባ የኢትዮጽያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መዲና፣ የዲፕሎማቲክ መቀመጫ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተሻለ መልኩ የሚስተዋልበት በመሆኑ ነው ብለዋል።
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጸጋዬ ሞሼ የቤት ልማት ፖሊሲ አስመልክቶ ባደረጉት ገለጻ የቤት ጉዳይ የማንነት እና የሰው ልጅ የክብር መገለጫ ሲሆን የቤት ልማት ፖሊሲ ፋይናንስ፣ መሬት፣ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ መጠቀም፣ ከተደራሽነት አንጻር፣ የቤት አስተዳደር መረጃ መያዝ እና ጠንካራ እና ተገማች የቤት ስርዓት መፍጠር እና መሰል የፖሊስው ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሆኑ በዝርዝር ገልጸዋል።